የጥምቀት በዓል ለሰው ልጆች ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ ስነ ጥበብ ማደግ ተፋቅሮና ተከባብሮ መኖር፣ ለቱሪስት መዳረሻነት፤ ለገጽታ ግንባነት ታላቅ ጠቀሜታን እያበረከተ ይገኛል፡-ቱሪዝም ሚኒስቴር

You are currently viewing የጥምቀት በዓል ለሰው ልጆች ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ ስነ ጥበብ ማደግ ተፋቅሮና ተከባብሮ መኖር፣ ለቱሪስት መዳረሻነት፤ ለገጽታ ግንባነት ታላቅ ጠቀሜታን እያበረከተ ይገኛል፡-ቱሪዝም ሚኒስቴር

AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም

የጥምቀት በዓል አከባበር ከዋናው የሀይማኖት መሰረታዊ ትርጉም ባሻገር በዓሉ ለሰው ልጆች ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ ስነ ጥበብ ማደግ ተፋቅሮና ተከባብሮ መኖር፣ ለቱሪስት መዳረሻነት፤ ለገጽታ ግንባነት ታላቅ ጠቀሜታን አበርክቷል እያበረከተም እንደሚገኝ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በዓሉን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የጥምቀት የአደባባይ በዓል በኢትዮጵያ በጥር ወር ከሚከናወኑ በዩኔስኮ ከተመዘገቡ የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው ያለው መግለጫው በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ከጥር 10 ጀምሮ የሚከናወን ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓት ነው ብሏል፡፡

የበዓሉ አከባበር ከዋናው የሀይማኖት መሰረታዊ ትርጉም ባሻገር በዓሉ ለሰው ልጆች ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ ስነ ጥበብ ማደግ ተፋቅሮና ተከባብሮ መኖር፣ ለቱሪስት መዳረሻነት፤ ለገጽታ ግንባነት ታላቅ ጠቀሜታን አበርክቷል እያበረከተም ይገኛል ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የጥምቀት በዓል በመላው ኢትዮጵያ የቤተ-ክርስቲያኗ ዶግማ ቀኖናና ትውፊት መሰረት አድርጎ እንደ የአካባቢው ባህልና ቋንቋ ሁኔታ እንደሚከበርም ጠቅሷል።

በተለይ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ፣ በጎንደር አጼ ፋሲል መዋኛ፣ በአክሱም ማይሹም፣ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ዩሐንስ አምባ ገጠርጌ ባህረ ጥምቀት፣ በባቱ ሀይቅ ላይ፣ በኢራንቡቲ፣ በከፍተኛ ድምቀት እንደሚከበር አመልክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ የጥምቀት በዓል ቱርፋቶች እንደሚከተለው አብራርቷል፡-

ብሔር፣ ባህል ቋንቋ ሳይለያይ በአንድ የሚከበር መሆኑ፤

በባዕሉ የወግ፣ የባህል አልባሳት፣ የእጅ ስራ ጥበባት የሚታዩበት ኢትዮጵያዊ ስንኝ፣ ግጥም ዜማ የሚማሩበት፣ የሚነገሩበት ትሩፋት መሆኑ፤

ሥርዓተ ወጉ ሳይፈልስ ወጣቱ ባህሉን፣ እምነቱን ወጉንና ክብሩን ተብቆ አስጠብቆ መቆየቱ፤

በየጊዜው በዓሉ መደብዘዝ ሳይታይበት እየደመቀ እየፈካ መከበሩ፤

የአገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኚ ቀልብና አይን መማረኩ፤

በዓሉ ጎብኚዎች የኢትዮጵያን የባህል አልባሳት፣ ሙዚቃ፣ አመጋገብን ጨምሮ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ወጎችን መጎብኘት እንዲችሉ እድል ይሰጣልም ብሏል ሚኒስቴሩ።

የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን እንቅስቃሴ ላይ በጎ አስተዋፅኦ በማበርከት ለአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ገቢ እንደሚያስገኝ ያመለከተው ሚኒስቴሩ ጥምቀት ሃይማኖታዊ በዓል ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶች ማሳያ ነውም ብሏል በመግለጫው፡፡

የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን የመሳብ ችሎታው ለአገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ወሳኝ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግም አብራርቷል።

በመሆኑም ጥምቀትን እና መሰል የማይዳሰሱ የአደባባይ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ በዓላትን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እና ሁሉም ሚዲያዎች በሚገባ በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ በቱሪዝም መዳረሻነት ስም በማጠናከር በታለመለት ጊዜ እውን ማድረግ ይችላል ሲል ሚኒስቴሩ ጠቅሷል።

ሚኒስቴር መሥሪያቤቱ የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በርካታ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በልዩ ሁኔታ በሚታደሙባቸው ጎንደር፣ ባቱ እና ኢራንቡቲ ከኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከአማራ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር እንደሚያከብር አመልክቶ በዚህና በመሰል በዓላት ሕብረተሰቡ እና ሚዲያዎች ልዩ ትዝታ ቀስቃሽ ምስሎችን በማስቀረት በየማህበራዊ ገጾቻቸው በልዩ ልዩ ሀገራዊ እና የውጭ ቋንቋዎች ምስሎቹን በማጋራት በጋራ የመስህብ ሀብቶቻችንን እናስተዋውቅ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review