AMN-ኅዳር 18/2017 ዓ.ም
የፈረንሳዩ ምግብ ማቀነባበሪያ ዴላሞት ኢንተርፕራይዝ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድረው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የደረቅ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጿል፡፡
ኩባንያው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ለመስራት ላሰበው ጣፋጭና ደረቅ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በዋናነት ከሚያስፈልጉ ግብአቶችን ውስጥ ስንዴ፣ የቅባት እህሎች እና የእንስሳት ተዋጽኦ መሆናቸውን የኩባኒያው መስራች ሴባስቲያን ዴላሞት አብራርተዋል፡፡
የኢዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኩባንያው ባለቤቶች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ኢትዮጵያ የስንዴ ምርቷን ለማሳደግ ከፍተኛ ስራ እየሰራች ባለበት ወቅት መሆኑን ጠቅሰው ሀገሪቱ በበጋ እና በመኸር ስንዴ ምርት ፍላጎቷን ከሟሟላት አልፋ ለውጪ ሀገር ገበያ ልታቀርብ ስራ በጀመረች ወቀት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዩክሬንና የራሽያ ግጭትን ተከትሎ በዓለም ላይ የተፈጠረው የስንዴ ምርት አቅርቦት መስተጓጎል ተጽእኖ እንዳያሳርፍባት መንግስት ቀድሞ በወሰደው ፈጣን እርምጃ ሀገሪቱ ከውጪ ስንዴ ለማስገባት ታወጣ የነበረውን ከ750 ሚሊየን ዶላር በላይ በሀገር ውስጥ መተካት መቻሏን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ስንዴ ምርት አቅርቦትን በበላይነት መምራት እንደቻለች ጠቁመዋል፡፡
ኩባኒያው የሚያስፈልገውን ምርት በኮንትራት ፋርሚንግ ቀጥታ ከአርሶ አደሮች ሊወስድ እንደሚችል ያብራሩት ደግሞ የኮርፖሬሽኑ ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ ናቸው፡፡
ለዚህ አይነቱ አሰራር ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው የፈረንሳዩ ብቅል አምራች ኩባንያ ሱፍሌት ጥሩ ምሳሌ መሆኑን ጠቅሰው ኩባንያው በኢትዮጵያ ላሉ ቢራ ፋብሪካዎች የሚያስፈልገውን ገብስ 70 ሺ ከሚደርሱ አርሶ አደሮች በኮንትራት ፋርሚግን ስርዓት እንደሚገዛ ጠቁመዋል፡፡
ኩባንያው በኢንዱሰትሪ ፓርኮች ውስጥ ፋብሪካውን ከተከለ ሊያገኝ የሚችለውን ከታክስ እና ከታክስ ውጪ ያሉ ማበረታቻዎችን እንደሚያገኝ ያብራሩት ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ባለሞያዎች የኩባንያውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ኩባኒያው ለሚያመርተው ምርት ግብዓት የሚሆኑ ጥሬ እቃዎችን ከኢትዮጵያ ከመጠቀም በተጨማሪ በዘርፉ ያካበተውን ቴክኒካል እውቀት ለኢትዮጵያ ባለሞያዎች በማስተለለፍ ለሀገራዊ ክህሎትና እወቀት መዳበር የበኩሉን ሚና መጫወት እንደሚፈልግም የኩባኒያው መስራች ጠቁመዋል፡፡
ኩባኒያው የምርት ሂደቱን በአግባቡ ለመከወን እስከ 10 ሺ ሜትር ስኩር የለማ መሬት እንደሚፈልግም መግለጻቸውን ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
All reactions:
4646