የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

You are currently viewing የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

AMN – ታኅሣሥ 12/2017 ዓ.ም

የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጥቁር ሕዝቦች ኩራት በሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘት ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ትግል መሥዋዕት ለከፈሉ ጀግኞች መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ፕሬዚዳንቱ የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸውንም ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ማክሮን በዚሁ ወቅት አዲስ አበባ ባሳየችው ፈጣን ለውጥ መደነቃቸውን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነችም በራሳቸው እና በከተማ አስተዳደሩ ለፕሬዚዳንቱ ስም ምስጋናቸውን አቀርብዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review