የአለም የአእምሯዊ ንብረት ቀን በአለም ለ25ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ23ኛ ጊዜ “ሙዚቃና አእምራዊ ንብረት ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በዓሉን በማስመልከት በሳይንስ ሙዚየም የፓናል ዉይይትና የፈጠራ ስራዎች አዉደ ርዕይ አዘጋጅቷል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልዱ ይመስል እንደገለጹት፣ የፈጠራና ኢኖቬሽን አቅምን የሚያረጋግጡ መብቶች በዲጂታል ስርዓት ዉስጥ የማስገባቱ ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የሙዚቃ፣ የቅጅ፣ የኪነ ጥበብ፣ የስነ ጽሁፍ፣ የብሮድ ካስቲንግ፣ ህትመትና ሌሎች መስኮች ከስራዎቻቸዉ የሚገባቸዉን ጥቅም እንዲያገኙና መብቶቻቸዉ እንዲጠበቁ የማድረጉ ተግባር ዉጤታማ መሆኑንም አቶ ወልዱ አመላክተዋል፡፡
በመድረኩም ላይ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የፈጠራ ቴክኖሎጂ አዉደ ርዕይ ቀርቧል፡፡
በሩዝሊን መሀመድ