AMN- ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም
የፊፋ ዋና ጸሃፊ ላርስ ኒልስ ማቲያስ ግራፍስትሮም እና የካፍ ሶስተኛው ምክትል ፕሬዝዳንት ሱሌማን ዋበሪ በ46ኛው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ መላኩ በዳዳ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።