የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከማእከል እስከ ወረዳ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ሊሰጥ ነው

You are currently viewing የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከማእከል እስከ ወረዳ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ሊሰጥ ነው

AMN-መስከረም 29/2017 ዓ.ም

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከማእከል እስከ ወረዳ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ በዘመቻ ሊሰጥ መሆኑ ተገለፀ።

የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራምና የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ተቋማት ይህን አስመልክተው በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ተቋማቱ በጋራ መስራታቸው ዲጂታል ስርአትን በተናበበ መንገድ ለማከናወን ነው ብለዋል የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ።

ከተማ አቀፍ የሞዝገባ ስራውን ለማሳለጥ ይረዳ ዘንድም ሁለቱ ተቋማት የጋራ ግብረሃይል አቋቁመው የቅድመ ትግበራ ስራዎች መጠናቀቃቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ዮዳሄ አርዓያሥላሴ ተናግረዋል።

የሲቪል ምዝገባ ስርአት ለመሰረታዊና ተአማኒነት ላለው የመረጃ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑም በጋዜጣዊ መግለጫው ተመልክቷል።

በዝናሽ ሞዲ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review