የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን በአራዳ ክፍለ ከተማ አራት ኪሎና ፒያሳ አካባቢ የተገነባውን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተዘዋውረው ጎበኘ

You are currently viewing የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን በአራዳ ክፍለ ከተማ አራት ኪሎና ፒያሳ አካባቢ የተገነባውን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተዘዋውረው ጎበኘ

AMN – ታኅሣሥ -8/2017 ዓ.ም

በፕላን ልማት ሚንስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ እና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ሚንስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ( ዶ/ር ) የተመራው የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በአራዳ ክፍለ ከተማ አራት ኪሎና ፒያሳ አካባቢ የተገነባውን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተዘዋውረው ጎበኝቷል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሐም ታደሰ፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ እንዲሁም የአራዳ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም የኮሪደር ልማቱንና የተጀመረውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ለሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት አስጎብኝተዋል ፡፡

የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራው ሲጠናቀቅ የወንዙን ህልውና በመታደግና የከተማዋን ገፅታ በመቀየር ነፋሻማና ለመኖሪያ ምቹ አካባቢን እንደሚፈጠር አስረድተዋል።

በተመሳሳይም አራት ኪሎ ፕላዛ የውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መንገድና ከአራት ኪሎ ፒያሳ መሀል የሚገኘው የራስ መኮንን የመስታወት ድልድይ ግንባታ ስራ ለከተማዋ ደረጃ የሚመጥን በመሆኑ ለሀገር ገፅታ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የሱፐርቪዥን ቡድኑ ማመላከቱን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review