የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት መደበኛ የዳኝነት ሥራ ጀመሩ

You are currently viewing የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት መደበኛ የዳኝነት ሥራ ጀመሩ

AMN -ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት መደበኛ የዳኝነት አገልግሎትን በይፋ ጀምረዋል።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተካሂዷል::

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በይፉ አገልግሎት መጀመራቸው ተገልጿል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፤ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ሆነው መቆየታቸውን ተናግረዋል።

በእነዚህ ጊዜያትም በተያዘው በጀት ዓመት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እንደ ሁልጊዜው ፍትሐዊ፣ ነጻና ገለልተኛ ሆነው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በአዲሱ በጀት ዓመት ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት የመስጠት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በፍርድ ቤቶች እየተተገበሩ የሚገኙ የለውጥ ስራዎች ፍትሐዊ፣ ነጻና ገለልተኛ አገልግሎት እንዲሰጡ እያስቻለ መሆኑም ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review