AMN- መስከረም 30/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ምክክሩ ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና እና ተሳትፎ ለማጎልበት ታሳቢ ያደረገ ውይይት ማካሄዱን አስታወቀ።
በውይይቱ የ45 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መሳተፋቸውን የገለጸው ኮሚሽኑ፥ መሰል ውይይቶች ሲያዘጋጁ ይህ ለ5ኛ ጊዜ ነው ብሏል።
መድረኩም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሀገራዊ ምክክሩ ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና እና ተሳትፎ ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብሏል፡፡
በውይይት መድረኩ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፥ ኮሚሽኑ ካለፈው የውይይት መድረክ ወዲህ የተከናወኑ ተግባራትን አስረድተው፥ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራትን ጠቁመዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም፥ ከሀገራዊ ምክክር መድረኩ ራሳቸውን ያገለሉ እና በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖች ወደ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች እገዛ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለከታል።