የ2ተኛዉ ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ተወዳዳሪዎች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን ጎበኙ

You are currently viewing የ2ተኛዉ ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ተወዳዳሪዎች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን ጎበኙ

AMN – ጥር- 24/2017 ዓ.ም

የ2ተኛዉ ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ተወዳዳሪ እንግዶች በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን ጎብኝተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በሚካሄደው ዓለም አቀፉ ዓመታዊ የቁርዓን እና አዛን ውድድር ላይ ለመሳተፍ 60 ሀገራትን ወክለው የመጡ ተሳታፊዎች የዓድዋ መታሰቢያን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጉብኝተዋል።

ተሳታፊዎቹ ከአፍሪካ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ከእስያ፣ ከአውሮፓ እና ከአሜሪካ የተወጣጡ ሲሆን ውድድሩ በዘይድ ኢብን ሳቢት የቁርዓን ማኅበርና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት የተዘጋጀው ነው።

የወድድሩ ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድም ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review