የ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሜር ሊግ ዛሬ ሲጀምር መሪው ሊቨርፑል አስቶን ቪላን ይገጥማል፡፡

You are currently viewing የ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሜር ሊግ ዛሬ ሲጀምር መሪው ሊቨርፑል አስቶን ቪላን ይገጥማል፡፡

AMN- የካቲት 12/2017 ዓ.ም

ምሸት 4 ከ 30 ሲል በቪላ ፓርክ ወሳኝ ጨዋታ ይደረጋል፡፡በዩናይ ኤምሪ የሚመራው አስቶን ቪላ የሊጉ መሪ ሊቨርፐልን መሪነቱን ለመግታት ይጫወታል፡፡

ከአራት አመት በፊት ሊቨርፑልን 7 ለ 2 ካሸነፈ በኋላ ካለፉት 9 ጨዋታዎች ድል ያልቀናው ባለ ሜዳው በዘንድሮ አመት ባለፉት 12 ጨዋታዎች በሜዳቸው ሽንፈት አልገጠማቸውም፡፡

ሁለቱ ክለቦች ምሽት ለ183ኛ ጊዜ የሚገናኙ ይሆናል፡፡ሊቨርፑል 92ቱን አስቶን ቪላ ደግሞ 52ቱን ጨዋታዎች በድል ተወጥተዋል፡፡

በቪላ በኩል አማካዩ ቦባከር ካማራ የረጅም ጊዜ ጉዳት ያለበት ሲሆን የሊዮን ቤሊ፤ ኤዝሪ ኮንሳና ማቲ ካሽ የመሰለፋቸው ጉዳይ አልተረጋገጠም፡፡

በአንጻሩ በቀያዮቹ በኩል ደግሞ ተከላካዩ ጆ ጎሜዝ ተጨማሪ ምርመራ የሚያስፈልገው ተጫዋች ነው፡፡ ኮዲ ካክቦ የመሰለፍ እድሉ አጠራጣሪ መሆኑ ተገልጻል፡፡

አሰልጣኝ ዩናይ ኤምሪ ሊቨርፑልን ከገጠሙባቸው 12 ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ያሸነፉበት መጥፎ ታሪክን ለመቀየር የሚያደርጉት ትልቅ መርሃ ግብር ነው፡፡

በሊጉ ለ21 ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት ያልቀመሰው ሊቨርፑል ከተከታዩ አርሰናል በ10 ነጥብ ለመለየት የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ሆኖ የሚያደርገው ሲሆን በቀጣይ ከማቸስተር ሲቲና ኒውካስትል ጋር ስለሚጫወትም ስንቅ ይዞ ለመውጣት ይፋለማል፡፡

በዮናስ ሞላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review