ዩናይትድ ኪንግደም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማሳደግ እንደምትፈልግ የዩናይትድ ኪንግደም የልማትና አፍሪካ ሚኒስትር አንድሪው ሚቼል ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኒው ዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን የዩናይትድ ኪንግደም የልማትና አፍሪካ ሚኒስትር አንድሪው ሚቼል ጋር ተወያይተዋል።
አንድሪው ሚቼል አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር ወደ ስትራቴጂክ ትብብር ደረጃ የማሳደግ ፍላጎት እንዳላት አመልክተዋል።
ይህም እርምጃ በሁለቱ አገራት መካከል በንግድ፣ የኢንቨስትመንት ደህንነት፣ በስደተኞችና በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ እ.አ.አ በሚያዚያ ወር 2024 በዩናይትድ ኪንግደም በሚካሄደው የአፍሪካ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ እንድሳተፍ መጋበዟን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ቁልፍ መልዕክዓ ምድራዊ ቦታ ላይ የምትገኝና በአፍሪካ ወሳኝ ሚና የምትጫወት አገር መሆኗን አንስተዋል።
አቶ ደመቀ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ እንድትሳተፍ የቀረበላትን ጥያቄ እንደምትቀብልና የስትራቴጂካዊ ትብብር ፍላጎቱንም በመልካም ጎኑ እንደምታየው መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ