ያለ ንፁህ መጠጥ ውኃ ከ200 ዓመታት በላይ በሰው አልባ ደሴት የኖሩት የፍየል ዝርያዎች

You are currently viewing ያለ ንፁህ መጠጥ ውኃ ከ200 ዓመታት በላይ በሰው አልባ ደሴት የኖሩት የፍየል ዝርያዎች

AMN – ሚያዝያ 07/2017

ያለ ንፁህ መጠጥ ውኃ ከ200 ዓመታት በላይ በሰው አልባ ደሴት የኖሩት የፍየል ዝርያዎች ዓለምን እያነጋገሩ ነው፡፡

የፍየል ዝርያዎቹ ላለፉት 250 ዓመታት በሰሜን ምስራቅ ብራዚል በእሳተ ጎሞራ በተፈጠረ ሰው አልባ ደሴት ውስጥ ሲኖሩ ቆይተዋል፡፡

ሳይንቲስቶች የፍየል ዝርያዎቹ ያለ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ከሁለት ምዕተ ዓመታት በላይ እንዴት በህይወት ሊቆዩ ቻሉ የሚለውን ለመመለስ ጥናት ጀምረዋል፡፡

ሰው አልባ በሆነችው ደሴት በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሱት የፍየል ዝርያዎቹ ጤናማ አካላዊ ዕድገት ያላቸው መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን ይበልጥ አስገራሚ አድርጎታል፡፡

ካለ ውኃ በህይወት የመቆየት አስደናቂ አቅምያላቸው የፍየል ዝርያዎቹ ፤ ቀድሞውኑ የሰው ጠረን ወደማታውቀው ደሴት እንዴት ሊመጡ እንደቻሉም ጥናቱ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቺኮ ሜንዴስ የተባለው የሀገሪቱ የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ተቋም በደሴቲቱ የሚኖሩትን የመጨረሻዎቹን 27 የፍየል ዝርያዎች ወደ ሳንታ ባርባራ የባህር ዳርቻ አካባቢ ማዘዋወሩን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review