የአሁኑ አፍሪካ ህብረት “የአፍሪካ አንድነት ድርጅት” በሚል በግንቦት ወር 1955 ዓ.ም. ተመሠረተ፤
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቀመጫውን በኢትዮጵያ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ አድርጎ በ32 የአፍሪካ ሀገራት ነው የተመሠረተው፤
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ነበሩ፤
“የአፍሪካ አንድነት ድርጅት” የአፍሪካ ህብረት ወደሚል ስያሜ የተቀየረው በሐምሌ ወር 1994 ዓ.ም ነው፤
የአፍሪካ ህብረት አሁን ላይ 55 አባል ሀገራት አሉት፤
የአፍሪካ ህብረት ፓን አፍሪካኒዝም (መላ አፍሪካዊነት) በሚል ለአፍሪካውያን ሁሉ የሚያገለግል ፓስፖርት ሥራ ላይ ለማዋል እየሰራ ነው፤