AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም
ዴንማርክ ለኢትዮጵያ ብልፅግና የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የዴንማርክ ልዕልት ቤንዲክት አስትራይድን አስታወቁ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፥ የዴንማርክ ልዕልት ቤንዲክት አስትራይድን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ጊዜ ልዕልት ቤንዲክት አስትራይድን፥ ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች እያካሄደች ያለውን የልማት ስራ አድንቀዋል።
ኢትዮጵያ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት አገራቸው ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው፥ ዴንማርክ የረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ወዳጅ መሆኗን አንስተዋል።
ሁለቱ አገራት ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በኢኮኖሚው መስክ የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩም ገልፀዋል።
ዴንማርክ በተለያዩ መስኮች እያደረገች ላለው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።