AMN-ጥር 5/2017 ዓ.ም
የዴንማርክ ልዕልት ቤንዲክቴ አስትራይድ በህፃናት ድጋፍና ክብካቤ ዙሪያ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚያከናውናቸውን ስራዎች ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ የዴንማርክ ልዕልት ቤንዲክቴ አስትራይድቹ ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይቱ ኢትዮጵያና ዴንማርክ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ እስካሁን የገነቡትን ውጤታማ የእርስ በርስ ግንኘኙኑት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሕጻናት ድጋፍ እና ክብካቤ፣ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ፣ በታዳጊ ሴቶች ትምህርት፣ በሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በነዚህና በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ተነሳሽነት ተናግረዋል።

የዴንማርክ ልዕልት ቤንዲክቴ አስትራይድ በበኩላቸው የተለያዩ የትብብርና የቅንጅት መስኮች ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር መንግስታቸው ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በህፃናት ድጋፍና ክብካቤ የተጀመሩ ስራዎችን እንደሚያስቀጥሉ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

All reactions:
8585