ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውዬ በምርመራ እያጣራሁ ነው – የአዲስ አበባ ፖሊስ

You are currently viewing ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውዬ በምርመራ እያጣራሁ ነው – የአዲስ አበባ ፖሊስ

AMN-ሚያዚያ 06/2017 ዓ.ም

ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆኑ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያስረጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቡ ሚሊዮን ድሪባ የሚባል ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስል በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸውን ያነሱበት ጉዳይ ሆኗል።

በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቡ በጎዳናዎች ላይ የተለያዩ አፀያፊ በተለይም የሴቶችን ክብር የሚነካ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች በመፈፀም የቀረፃቸውን ምስሎች በመልቀቅ በፈፀመው ህገ ወጥ ተግባርና በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ ይገኛል።

በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ አንዳንድ ምስሎች ተገቢነታቸውን የሳቱና ያፈነገጡ እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ ገልፆ፤ ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በሚለቁ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review