ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

You are currently viewing ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በ2017 በጀት ዓመት የሚገለገልባቸውን ዕቃታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ በዚህም መሠረት፡-

ሎት 1. Video camera & Accessories ግዥ
ሎት 2. ዲጂታል መታወቂያ እና ባጅ ማተሚያ ማሽን ግዥ
ሎት 3. C-Band 5G LNB & Band pass Filter ግዥ
ሎት 4. መኪና ላይ የሚገጠም GPS ግዥ
ሎት 5. Portable LED video Wall Screen ግዥ

በጨረታ ቁጥር ኢሚ.ኔ.ብ.ግ.ጨ.001/2017 በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የገቢዎች ክሊራንስ ያላቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና በግዥ እቅራቢነት የተመዘገቡ።
  3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለእያንዳንዱ ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ/ ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አመስት መቶ ሺህ/ ለሎት 3 ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ/ ለሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ/ ለሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1 – 5 ላሉት ጨረታዎች 10 የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ቢሮ ቁጥር 28 የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  6. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 34 ይከፈታል። ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም። የመክፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሐሳባቸውን ዋናውን እና ኮፒውን /ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጂናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  8. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
  9. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመሥሪያ ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል።
  10. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ጀረባ ያለው ሕንፃ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ 011-1-1116382 መደወል ይችላሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review