ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጠናቀቀውን የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ-ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ስራን ተመለከቱ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጠናቀቀውን የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ-ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ስራን ተመለከቱ

AMN-ሰኔ 01/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ-ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሥራ ዛሬ ተመልክተዋል።

የኮሪደር ልማት ሥራው 8 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 4 ኪሎሜትር የብስክሌት መጋለቢያ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ሱቆች፣ በመላው ከተማዋ እንደተገነቡት ያሉ የተለያዩ ዘመናዊ የሕዝብ መገልገያዎች ግንባታን ያካተተ ነው።

ይኽ ለውጥ በከፍተኛ የፍሰት መጨናነቅ በሚታወቀው ከባቢ በእጅጉ ሲፈለግ የነበረውን የፍሰት መሻሻል እና የኑሮ ደረጃ ከፍታ የሰጠ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review