ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተከፈተው የ2017 “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ከወትሮው በተለየ አጠቃላይ 288 አቅራቢዎች ምርታቸውን አቀረቡ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተከፈተው የ2017 “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ከወትሮው በተለየ አጠቃላይ 288 አቅራቢዎች ምርታቸውን አቀረቡ

AMN – ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተከፈተው እና ለ5 ቀናት የሚቆየው የ2017 “ኢትዮጵያ ታምርት” ወይም ‘Made in Ethiopia’ ኤክስፖ፣ ከወትሮው በተለየ አጠቃላይ 288 አቅራቢዎች ምርታቸውን አቅርበዋል፡፡

የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ወይም ‘Made in Ethiopia’ ንቅናቄ ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ ተስፋ ሰጭ ውጤቶች ማስገኘቱም ተገልጿል፡፡

በጥቂቱም፡-

• ዓመታዊ የዘርፍ ዕድገት በ2014 በጀት ዓመት 4.8 በመቶ የነበረው በ2016 በ8.4 በመቶ አድጓል። በያዝነው የበጀት ዓመት( 2017) በ12 በመቶ ያድጋል ተብሎ ተተንብዮአል፡፡

• የማምረት ዐቅም አጠቃቀማችን በ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት ወደ 61.2% አድጓል፤

• ገቢ ምርት በመተካት በ2014 በጀት ዓመት የነበረው 2.1 ቢሊዮን ዶላር በ2017 9 ወራት ወደ 3.1 ቢሊዮን ዶላር አድጓል፡፡

• የማኑፋክቸሪንግ የኃይል ፍጆታ በ2015 ከነበረበት 3.88 ቢሊዮን ኪሎዋት ሰዓት በ2016 ወደ 4.67 ቢሊዮን ከፍ ብሏል

• የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የብሔራዊ አካውንት መረጃ እንደሚያሳየው(National Account) የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዕሴት ጭማሪ ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል፤ይሄም የማኑፋክቸሪንግ ዕሴት የተጨመረበት ምርት በ2014 በጀት ዓመት ከነበረበት 5.3 ቢሊዮን ዶላር ገደማ፤ በ2016 ወደ 9.25 ቢሊዮን ዶላር አድጓል። ይህ ከፍተኛ የሆነ ዕሴት ጭማሪ ከላይ የተጠቀሰውን ትክክለኛ የምርት ዕድገት የሚያንፀባርቅ ነው።

በቀጣይ ዓመታት ለአግሮ ፐሮሰሲንግ መስፋፋት የሚያግዙ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ማሽኖችን ፣ በገጠር የመስኖ እና የቤት ውሰጥ ኃይል አቅርቦት ችግሮችን የሚፈቱ የነጻ ኃይል ማምረቻ ማሽኖችን፣ እንዲሁም ፈጠራን ማበረታትና አዳዲስ ምርቶችን ወደ ገበያ የማቅረብ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review