AMN – የካቲት 9/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ልማት ማዕከል ዳይሬክተር እና የተመድ ዘላቂ ልማት ሶሉሽንስ ኔትወርክ ፕሬዝዳንት ከፕሮፌሰር ጀፍሪ ዲ. ሳችስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ጎን ለጎን የተደረገው ውይይት በተለያዩ የልማት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኤክስ ገጻቸው ገልጸዋል፡፡