AMN – ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር ያደረጉበት ”የተጠናከረ የባለብዙወገን ግንኙነት ለሚዛናዊ የአለም ልማት እና ደኅንነት” በሚል ጭብጥ የ16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ዝግ ስብሰባ ዛሬ ጠዋት መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 ወደብሪክስ እንዲቀላቀሉ ከተጋበዙት ሀገራት መካከል መሆኗን ያስታወሰው ጽህፈት ቤቱ ከጥር 2024 ጀምሮም የአባልነት እንቅስቃሴ በይፋ መጀመሩን ገልጿል።