AMN- ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና ጸሐፊውን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ሲሉ እንደተቀበሏቸው እና በተለያዩ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።