AMN_የካቲት 18/2017 ዓ.ም
ሚኒስቴሩ የእናቶች እና ህጻናት ጤና እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አገልግሎትን ማሳደግ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉደዮች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከሌሎች የስራ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ከጌትስ ፋውንዴሽን በጤና ላይ የሚሰሩ 15 የጤና ቡድኖች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በመድረኩ የጤና ሚኒስቴር ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ዶ/ር መቅደስ፣ በአጋሮች የሚተገበሩ ፕሮግራሞች ከጤና ሚኒስቴር እና ብሄራዊ ስትራቴጂዎች ጋር የተናበቡ መሆን አለባቸው ብለዋል።
የማህበረሰብ ተሳትፎን በማሳደግ በሽታን መከላከል እንደሚገባም አንስተዋል።
በውይይት መድረኩ የጤና ፋይናንስ፣ የቤተሰብ እቅድ፣ ተዋልዶ ጤና፣ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን፣ እና ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።