AMN – የካቲት 5/2017 ዓ.ም
የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን የተካው እና በ2002 በአዲስ አበባ መሰረት የጣለው የአፍሪካ ህብረት ከ50 በላይ አባል ሀገራትን በማቀፍ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡
የህብረቱ ዋነኛ አላማዎች የአፍሪካ አንድነትን ማበረታት ፣ የአፍሪካ ሀገራት ውስጣዊ ችግሮችን መፍታት እንዲሁም አፍሪካ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላትን መብት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሲሆን ከነዚህ ዓላማዎች በመነሳት ህብረቱ ምን ምን ስኬታማ ተግባራትን አከናወነ ?
- በአህጉሪቱ አፍሪካዊ ተቋም እንዲኖር አስችሏል
የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚው የአፍሪካውያን መድረክ ሆኖ ያገለግላል ÷መንግስታት ፖሊሲዎቻቸውን እና ውሳኔዎቻቸውን ቁልፍ በሆኑ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ለማንፀባረቅና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ አገልግሏል ፡፡
ህብረቱ አፍሪካዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና የጋራ አቋም ለመውሰድ የሚያስችል ሲሆን በውስጣዊ ጉዳዮች ላይ የሚካሄዱት ስብሰባዎች የአፍሪካ መንግስታት በውስጥ ጉዳዮቻቸው፣ በተቋማቶቻቸው ዙሪያ በመምከር በፖለቲካው ረገድም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ድጋፍን ለማሰባሰብ ግዛል ፡፡
በአለምአቀፍ መድረኮችም በመድረኮቹ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ አፍሪካዊ አጀንዳ ለማስያዝ እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባሉ ጉባኤዎች ለአፍሪካ አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ ይህም አፍሪካውያን ድምፃችንን ማሰማት እንድንችል ብሎም የአፍሪካ መንግስታት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አስችሏል፡፡ በዚህም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአፍሪካ ድምጽ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ያላቸው ተቀባይነት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ይገኛል፡፡
- የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት
በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የትርክት ሞኖፖሊ የተቆጣጠሩት ጸረ-ምዕራብ እና ፀረ-ሊበራሊዝም የፖለቲካ አስተሳሰቦች ሲሆኑ ይህን በፓን አፍሪካኒዝም እና በአህጉራዊ አንድነት የበላይነት እንዲተካ በማድረግ የዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት እሴቶች እንዲከበሩ ተደርጓል ፡፡
እ.ኤ.አ. በ2001 ፣ በ1990 ዎቹ መጨረሻ እና በ 2000 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ከፓንአፍሪካንና ከኒዮ ሊብራሊዝም አማራጭ ጋር በተያያዘ በምሁራን መካከል ሰፊ ክርክር ተደርጓል ፡፡
በዚህ ረገድ የአፍሪካ የፓን አፍሪካኒዝም ምሁርና አባት የጋናው ክዋሜ ንክሩማህ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ እንግዳ እንዳልነበር ይከራከሩ ነበር፡፡
የናይጄሪያው ኦሊሴን ኦባሳንጆ እና የደቡብ አፍሪካው ታቦ ምቤኪም በዚህ ክርክር ተሳታፊ ነበሩ አፍሪካ ኅብረት ይህንን አስተሳሰብ በመቀየር ረገድ የራሱን አስተዋፅኦ አበርክቷል።
ከዛን ጊዜ በኋላ የአፍሪካ ህብረት የሊበራል እሴቶችን የስራው መሰረት አድርጎ ይመለከታቸዋል፡፡ አብዛኛው የአፍሪካ ሀገራትም የሊበራል እሴቶችን እንደ ብቸኛ መርህ አርገው ይወስዱታል ፡፡
አፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ. ጥር 2009 የአፍሪካ የዲሞክራሲ፣ የምርጫ ፣ እና አስተዳደር ቻርተሮችን አፅድቋል ፡፡
በቻርተሩም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት እና ዲሞክራሲያዊ ኋላቀርነትን ጨምሮ ለአፍሪካ የአስተዳደር ፈተናዎች እንዲሁም በአባል ሀገራት ሰላም በመፍጠር ረገድ የተለያዩ ድንጋጌዎችን አስቀምጧል ፡፡በዚህም ኅብረቱ በአፍሪካ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
ህብረቱ መፈንቅለ መንግስትን በመከላከልና በማስቀረት በሀገራት መካከልና በውስጣቸው የሚፈጠሩ ግጭቶችን በማስወገድ ረገድ ተጠቃሽ የሚባሉ የአመለካከት ለውጦችና ተግባራትን አከናውኗል ፡፡
- ደንቦችን ማውጣት
አፍሪካዊ ህጎች እና ፖሊሲዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ደንቦች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም እንዳላቸው ይታመናል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት አገራዊ ቅርጽ ያላቸው ዓለም አቀፍ ሕጎችን በማውጣት ረገድ በጣም ስኬታማ ስራ ሰርቷል።
ለአብነትም ዓለም አቀፍ ወንጀል እና ሽብርተኝነትን መዋጋትና መከላከል ፣ ወረርሽኞችን በጋራ መቆጣጠር ፣የተፈጥሮ የአደጋን መከላከል ፣ የንግድ እና የውጭ ዕዳ ጋር የተያያዙ ድርድሮችን የተመለከተ ፣የምግብ ደህንነት በማረጋገጥ፣ የስደተኞች የተፈናቃዮች አስተዳደር በተመለከተ ተጠቃሾች ናቸው ፡፡
- ግልፅና መደበኛ አሰራሮችን መከተል
የአፍሪካ ኅብረት አንዳንድ ህጎችን ወደ መደበኛ ህግ እንዲቀየሩ ማድረጉ በስኬት የሚነሳለት ሌላው ተግባር ነው።
ስኬታማና ወደ ተግባር ተለውጠው መደበኛ ህግ ከሆኑ ህጎች መካከል ፀረ-መፈንቅለ መንግስት ህግ ተጠቃሽ ነው በዚህ ረገድ በበርካታ ሀገራት የተሞከሩ የመፈንቅለ መንግስት ተግባራትን መቀልበስ ተችሏል ፡፡እ.ኤ.አ. በ2013 የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም ረገድ ጠንካራ አቋም የወሰደ ብቸኛው ዓለም አቀፍ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት እንደነበር ይታወሳል ፡፡
ከዚህ በተቃራኒም አንዳንድ የአፍሪካ ኅብረት ደንቦች ከመተግበር ወደኋላ የሚመለሱበት ጊዜያት አሉ ፡፡ለምሳሌ የፓን አፍሪካዊው የአንድነት ደንብ፣ በሰብአዊ መብት ረገጣ ረገድ የሚኖረው ተጠያቂነት ተጠቃሾች ናቸው።
- የአፍሪካ መንግስታትን ተግባራት መቆጣጠር
የአፍሪካ መንግስታትን ዋና ዋና ተግባራት በመቆጣጠር ረገድ የአፍሪካ ህብረት ያደረገው ጥረት አመርቂ ስኬቶች ባያስመዘግብም በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሚተላለፉ ውሳኔዎችን አፈፃፀም የማስተባበር እና የመቆጣጠር ተግባራት እንዲጎለብቱ የማድረግ ፣ የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት የአፍሪካ ኅብረት ፕሮግራሞችን እንዲተገብሩ የመርዳት እና ፖሊሲዎችን ተግባራዊ ያላደረጉ መንግስታትን በማገዝ እንዲያከናውኗቸው የሚደረጉ ጥረቶች ተጠቃሾች ናቸው ፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በህብረቱ የሚወጡ ህጎች መንግስታት በህጋቸው ውስጥ ማካተታቸውን ማረጋገጥ ፣ የሥርዓተ-ፆታ ጉዳይ በህብረቱ በሁሉም መርሃ ግብሮች እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንዲካተት ማድረግ ፣ የተከናወኑ ተግባራት በየዓመቱ ሪፖርት ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ለውጦች ናቸው፡፡
ምንጭ ፡- የአፍሪካ ህብረት ድረ ገፅ እና የምዕራብ ኦንታሪዮ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ቶማስ ከዋሲ ቲኩ ጥናት
በሽመልስ ታደሰ