በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፈው የጋዛ የሰብዓዊ እርዳታ ፋውንዴሽን በጋዛ ውስጥ እርዳታ ማከፋፈል ጀምሯል።
መቀመጫውን በጄኔቫ ያደረገው የሰብአዊ እርዳታ ቡድን፣ በማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ላይ ደህንነትን በማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ 90 ቀናት ውስጥ 300 ሚሊየን ሰሀን ምግቦችን ለመመገብ ቃል ገብቷል።
ፋውንዴሽኑ ምንም እንኳን እርዳታውን ለማስተጓጎል ያለመ ዛቻ ከሃማስ እየደረሰኝ ነው ቢልም፣ ዛቻው ድጋፉን ከማድረግ እንደማያግደው እና በየእለቱ የእርዳታ አቅርቦቶችን ማሳደግ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
ሆኖም በእርዳታ ስርጭቱ የፍልስጤም ተሳትፎን በሌለበት ከእስራኤል ጋር አብረው መስራት ድጋፉ እንደ መሳሪያ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል በሚል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች አብረው ለመስራት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መግለፃቸውን አር ቲ ኢ ዘግቧል።
በሊያት ካሳሁን