ፒኤስጂ እና ቦሩሽያ ዶርትሙንድ ለሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ደረሱ

ፒኤስጂ እና ቦሩሽያ ዶርትሙንድ ለሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ደረሱ

AMN – ሚያዝያ 07/2016 ዓ.ም

ዛሬ ምሽት በተደረጉ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ፒኤስጂ ባርሴሎናን እንዲሁም ቦሩሽያ ዶርትሙንድ አትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሰዋል።

በመጀመሪያው የደርሶ መልስ ጨዋታ በስፔኑ ባርሴሎና ክለብ በሜዳው 3 ለ 2 ተሸንፎ የነበረው የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ወደ ካምፕ ኑ ተጉዞ 4 ለ 1 በድምሩ 6 ለ 4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

የጀርመኑ ቦሩሽያ ዶርትመንድ በበኩሉ በስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ ከሜዳው ውጪ 2 ለ 1 ተሸንፎ የነበረ ቢሆንም በሜዳው 4 ለ 2 በድምሩ ደግሞ 5 ለ 4 በሆነ ውጤት አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል።

በዮናስ በድሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review