ፒያሳ ደጃች ዉቤ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

Exif_JPEG_420

AMN-ኅዳር 16/2017 ዓ.ም

አራዳ ክፍለ ከተማ ደጃች ዉቤ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ስራ ድርጅት ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ፣ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትና ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍ ያለ ርብርብ አድርገዋል።

Exif_JPEG_420

የእሳት አደጋው ዛሬ ከቀኑ 9:00 አካባቢ የተነሳ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፤ የእሳት ቃጠሎው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።

እሳቱ የተከሰተበት ቦታ አሽዋ ፣ ጠጠርና መሰል የኮንስትራክሽን ምርቶች ያሉበት ቦታ መሆኑ የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች በቀላሉ ወደ ቦታው እንዳይገቡ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

በካሳሁን አንዱ ዓለም

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review