ፓርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች በትብብር ለመስራት ፍላጎት አላት-የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትር

You are currently viewing ፓርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች በትብብር ለመስራት ፍላጎት አላት-የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትር

AMN – ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

ፓርቹጋል ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትር ኑኖ ሳምፓዮ ገለጹ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፓርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይና የትብብር ሚኒስትር ኑኖ ሳምፓዮ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርትና በሌሎችም መስኮች ያላትን የትብብርና የወዳጅነት ግንኙነት አጠናክሮ የማስቀጠል ፍላጎት አላት፡፡

የአገራቸው መንግስት በትምህርትና በባህል ዘርፍ ያለውን ወዳጅነትና የትብብር ግንኙነት በማስፋት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል የማሳደግ ፍላጎት እንዳለውም ሚኒስትሩ ኑኖ ሳምፓዮ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው በኢትዮጵያና በፖርቹጋል መንግስታት መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ከሚኒስትሩ ጋር በዝርዝር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎችም በሁለቱ አገራት መካከል የአካዳሚክ ትብብሮች በሚጠናከሩበትና አሁን ያለው ግንኙነትን በሚሰፋበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሙዚየም እያቋቋመ በመሆኑ ፖርቹጋል በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ የነበራትን ተሳትፎና ታሪክ ልታኖር እንደሚገባም ሚኒስተሩ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉዊዛ ፋራጋሶ በበኩላቸው አገራቸው የፖርቸቹጋል ብሄራዊ ቀንን ምክንያት በማድረግ በያሬድ የመዚቃ ትምህርት ቤት የባህል ትርኢት የማቅረብ ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review