
AMN ሚያዝያ 30/2017
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳን ታዬ አፅቀሥላሴ በነገው ዕለት በሚከበረው 80ኛው የሩሲያ የድል በዓል ላይ ለመታደም ዛሬ ማለዳ ሞስኮ ገብተዋል።
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃቱን ተከትሎ በተለይም ደግሞ የቀድሞው ሶቪየት ኅብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀውን ድል በማሰብ ነገ በሩሲያ መዲና ሞስኮ ለ80ኛ ጊዜ ለሚከበረው በዓል፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአለም መሪዎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኢዜአ ከስፍራው እንደዘገበው፤ የበርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የቻይና እና የብራዚል ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ በዚሁ የድል በዓል ላይ ይሳተፋሉ።
ከ80ኛው የሩሲያ የድል በዓል ተሳትፎ ጎን ለጎን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከተለያዩ አካላት ጋር የሁለትዮሽ እንዲሁም ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።