ፕሬዚዳንት ትራምፕ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ሊገዛ እየተደራደረ መሆኑን ገለጹ

You are currently viewing ፕሬዚዳንት ትራምፕ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ሊገዛ እየተደራደረ መሆኑን ገለጹ

AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ቲክቶክን ለመግዛት ውይይት ላይ እንዳለ እና በማህበራዊ ሚዲያው ሽያጭ ላይ የሚደረጉ ፉክክሮችን ማየት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ግዙፉ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ለጨረታ ዝግጁ ስለመሆኑ በጋዜጠኞች የተጠየቁት ፕሬዚዳንቱ፣ “አዎን” በሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ በርካታ ኩባንያዎችም ቲክቶክን ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸውን አክለዋል፡፡

ትራምፕም ሆኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከብሔራዊ ደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ የቻይናው ኩባንያ ቲክቶክ እንዲሸጥ ለዓመታት ግፊት ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

በአሜሪካ 170 ሚሊየን ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ መተግበሪያ እንዲታገድ ባለፈው ሳምንት የባይደን አስተዳደር ያሳለፈውን ውሳኔ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለ75 ቀናት እንዲራዘም ማዘዛቸው ይታወሳል፡፡

ለቲክቶክ የተጣለበት እገዳ ለ75 ቀናት እንዲራዘም የፈቀዱት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ባይትዳንስ መተግበሪያውን እንዲሸጥ ግፊት ያደረጉ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት እንዳደረጋቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review