ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

You are currently viewing ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

AMN- መስከረም 7/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ በመልዕክታቸው ፕሮፌሰር በየነ ለሀገራችን ዲሞክራሲን በመሻት ከታገሉት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ናቸው ብለዋል።

ሠላማዊ ትግልን፣ የሃሳብ የበላይነትንና ሃሳብን መሞገት የፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅት ለማሳየት እንደጣሩም መግለፃቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ለቤተሰባቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review