ሀረር የአለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል ሆነች

You are currently viewing ሀረር የአለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል ሆነች

AMN – ሚያዝያ 07/2017

ሆንግ ኮንግ በተካሄደው የአለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን ጉባኤ ሀረር ከተማ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።

የሃረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ሀረር ከተማ የፌደሬሽኑ አባል መሆኗ ሀረርን ከሌሎች ከተሞች ጋር ለማስተሳሰር እና አብሮ ለመስራት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023 ሀረር የአለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆኗ መመዝገቧ ይታወቃል። የሀረር የማንሰራራት ዘመን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review