ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላሟ የተረጋገጠና በኢኮኖሚ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑን የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ ተሳታፊዎች ተናገሩ

You are currently viewing ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላሟ የተረጋገጠና በኢኮኖሚ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑን የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ ተሳታፊዎች ተናገሩ

AMN ግንቦት 24 /2017

በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከግንቦት 22 እስከ 24 ቀን 2017 የተካሄደው የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ተጠናቋል።

ተቋማቱና ማህበራቱም ለኮሚሽኑ እንዲቀርቡ የለዯቸውን አጀንዳዎች ያስረከቡ ሲሆን አጀንዳዎቹንም ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ እና ኮሚሽነር ዶክተር አምባዬ ኡጋቶ ተረክበዋል።

የምክክሩ ተሳታፊዎች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፥ ሀገራዊ ምክክር የማያግባቡ ጉዳዮችን ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

የምክክሩ ተሳታፊ ሰዒድ ቃሲም፥ ምክክሩ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማረጋገጥ የሚያስችል ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ምክክሩ ለሀገራዊ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ በመስጠት የተረጋጋችና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ተናግሯል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊ ፋጡማ ሁሴን በበኩላቸው፥ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ለሀገር ዘላቂ ዕድገት መሠረት የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስለዚህም ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በምክክሩ ሂደት በመሳተፍ ለሀገር ዘላቂ ልማት የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ትልቅ አጋጣሚ በመሆኑ ሁሉም በነቂስ ሊሳተፍበት እንደሚገባ የገለጹት ግድሞ የመድረኩ ተሳታፊ አባገዳ ሰቦቃ ለታ ናቸው፡፡

የመድረኩ ተሳታፊ ሱልጣን ቱሲ በሰጡት አስተያየትም፥ሀገራዊ ምክክሩ አንድነትን፣አብሮነትን እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን እውን የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክሩን ሁሉም ኢትዮጵያ ሊጠቀምበት የሚገባ ትልቅ ዕድል መሆኑን ጠቁመው፥ ሁሉም ሀሳቡን በነጻነት ወደ መድረክ ሊያመጣ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊ ኢልሃን መሀመድ ሀገራዊ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ በመሆኑ ለስኬታማነቱ ያልተቆጠበ ትብብር ሊደረግ እንደሚገባ ተናግራለች፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ በምክክር የጋራ መግባባት የመፍጠር ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመው፤ ሁሉም ሊጠቀምበት እንደሚገባም ገልጻለች፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review