ሀገራዊ ምክክሩ የማያግባቡ ችግሮችን በመፍታት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሁነኛ መፍትሔ ነው መሆኑን ተሳታፊዎች ተናገሩ

You are currently viewing ሀገራዊ ምክክሩ የማያግባቡ ችግሮችን በመፍታት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሁነኛ መፍትሔ ነው መሆኑን ተሳታፊዎች ተናገሩ

AMN ግንቦት 22/2017

ሀገራዊ ምክክሩ የማያግባቡ ችግሮችን በመፍታት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሁነኛ መፍትሔ በመሆኑ ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የፌዴራል የተቋማትና ማህበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ለሀገር ዘላቂ ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በማስመልከትም የመድረኩ ተሳታፊዎች ለኢዜአ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከልም ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ፤ ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ትልቅ አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡

ለዘመናት ስር የሰደዱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመው፤ ለሀገር ዘላቂ እድገት የሚበጅ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ችግሮችን በምክክር የመፍታት ባህልን የሚያጎለብት ብሎም ዘላቂ ሰላምን ማስፈን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጀመረው አግባብ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠቆማቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሌላኛው የመድረኩ ተሳታፊ አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ እንዳለውም፤ ለሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ስኬታማነት የበኩሉን በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡

ሀገራዊ የምክክር ሂደት የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን ጠቁሞ፤ ለሀገር ዘላቂ እድገት የሚበጁ አጀንዳዎችን ለማቅረብ መዘጋጀቱንም ተናግሯል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊ ኦሞድ ኢታንግ፥ ሀገራዊ የምክክር ሂደት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መግባባት መፍጠር የሚያስችል ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እየተካሄደ በሚገኘው የፌደራል ተቋማትና ማህበራት የአጀንዳ ማሰባሰብ ከ38 ተቋማትና ማህበራት ተወካዮች በመሣተፍ ላይ ሲሆኑ የዛሬ የተጀመረው የምክክር ምዕራፍ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2017 የሚካሄድ ይሆናል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review