AMN-የካቲት 15/2017 ዓ.ም
የምክክር መድረኩን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ እና የቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ እየመሩት ይገኛል።
በመድረኩ የሲዳማ ክልል የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አስፋው ጎኔሶ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬን ጨምሮ የክልል እና የከተማ አመራር አካላት ተገኝተዋል።
በመድረኩም የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ የከተማዋን የልማት ስራዎች የሚያንፀባርቁ ስራዎችን የያዘ ሪፖርት ማቅረባቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።