ሀገር የሚቀየረው በአቋም እና ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ በመሆን ነው – ሙዓዛ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

You are currently viewing ሀገር የሚቀየረው በአቋም እና ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ በመሆን ነው – ሙዓዛ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

AMN-ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

ጊዜ፣ ጉልበት፣ እውቀትና ምቾታቸውን ለሀገራዊ ለውጥ መስዋዕት ያደረጉ ዜጎች ያለ ጥርጥር እራሳቸውንም ሀገራቸውንም ወደ እድገት ማማ ማድረሳቸው አይቀሬ ነው፡፡ ጥቂት አሥርት አመታትን ብቻ ሁለንተናዊ ዋጋ በመክፈል ሀገራቸውን ከድህነት ያወጡ ዜጎች ዛሬ ቀና ብለው በኩራት ሲናገሩ የማየታችን እውነትም ከዚሁ ይመነጫል፡፡

ቻይና፣ ሲንጋፖር፣ ታይዋን እና ደቡብ ኮሪያ ለዚህ ሁነኛ አብነቶች ናቸው፡፡ የዛሬ ከፍታቸው የትናንት የፀና የመለወጥ አቋሟቸው እና የከፈሉት ዋጋ ውጤት ነው፡፡

ኢትዮጵያም ለውጥ ጀምራ ይህንኑ ለማጽናት ዋጋ በመክፈል ጉዞ ከጀመረች ወዲህ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ታይተዋል፡፡ባልተለመደ መልኩ በአመራሩ ዘንድ የተስተዋለው ትጋት እና የዜጋው ቅንጅትም የእድገት ጉዞን ለማረጋገገጥ የሚያስችል ነው፡፡

ይህን መሰሉ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም በየወቅቱ ለአመራሩ ሥልጠናዎች እየተሰጡ ይገኛል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “የመጀመሪያው እውቀት ሀገርን መውደድ ነው፣ ሀገሩን የሚወድ ዜጋ የሀገሩን ሀብት እና ፀጋ ሰፍሮ የሚያውቅ ነው።” ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች እየሰጡት ባለው ሥልጠና ላይ ተናግረዋል፡፡

ሥልጠናው አመራሩ አቋሙን አፅንቶ አቅምን በመጠቀም ሀገሩንና አከባቢውን ለመለወጥ በቁርጠኝነት እንዲሰራ የሚያስችል ነው፡፡

አሰባሳቢ ትርክትን መገንባት እና ብሄራዊ ጥቅምን ማስከበር ደግሞ የሁል ጊዜም ተግባሩ ሊሆን ይገባል፡፡ አመራሩ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማስጠበቅ እና የብልጽግና እሳቤዎችን በመተግበር ታሪካዊ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም አማካሪው አሳስበዋል፡፡

በፕሮግራሙ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በበኩላቸው በቁጭት የጀመርናቸው ሀገራዊ ስኬቶቻችንን በማስቀጠል የተጣለብንን ኃላፊነትን መወጣት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ጊዜው የተጣለብንን ታሪካዊ ሀላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ እና ዋጋ መክፈልን የሚጠይቅ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review