ሁሉን ያካተተ ልማትን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን- የዩኤንዲፒ (UNDP) የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር

You are currently viewing ሁሉን ያካተተ ልማትን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን- የዩኤንዲፒ (UNDP) የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር

AMN-የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዓለም የልማት ፕሮግራም ረዳት ዋና ፀሃፊ እና የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተሯ አሁና ኢዚያኮንዋ ጋር ዛሬ ማለዳ መወያየታቸው ይታወሳል፡፡

ዳይሬክተሯ የነበራቸውን ቆይታ አስመልክተው በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ በኢትዮጵያ የስማርት ከተሞች ኢንቨስትመንት ጥረት ዙርያ ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር መወያየታቸውን ገልፀዋል፡፡

ዩ.ኤን.ዲ.ፒ ለሰው ልጆች ክብርና ፍላጎት ቅድሚያ የሚሰጥ ሁሉን አካታች ልማትን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውንም አስፍረዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review