ሃማስ አዲሱን የአሜሪካ የተኩስ አቁም ዕቅድ እንደማይቀበል አስታወቀ

You are currently viewing ሃማስ አዲሱን የአሜሪካ የተኩስ አቁም ዕቅድ እንደማይቀበል አስታወቀ

AMN- ግንቦት 22/2017 ዓ.ም

ሃማስ አዲሱን የአሜሪካ የጋዛ የተኩስ አቁም ዕቅድ እንደማይቀበል አስታውቋል።

ታጣቂ ቡድኑ በእስራኤል ይሁንታ ያገኘውን አዲሱን የአሜሪካ የተኩስ አቁም እና ታጋቾችን የማስለቀቅ ዕቅድ ውድቅ ማድረጉን ቢቢሲ ከአንድ የሃማስ ከፍተኛ ሹም አረጋግጫለሁ ብሏል።

ዋይት ሀውስ እስራኤል በአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ የቀረበውን የሰላም ዕቅድ ትናንት መፈረሟን ገልጿል።

አሜሪካ በጉዳዩ ላይ ከሃማስ ይፋዊ ምላሽ እየጠበቀች መሆኗን ማስታወቋን ተከትሎ ቡድኑ የቀረበው ዕቅድ ለጥያቄዎቼ አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ አይደለም በሚል ስምምነቱን ውድቅ አድርጎታል።

የእስራል ሚዲያዎች ለ60 ቀናት በሚቆየው የተኩስ አቁም ስምምነት ሃማስ 10 በህይወት ያሉ ታጋቾችን እንዲሁም 18 የሞቱ ታጋቾችን አስክሬን በሁለት ዙር ለመመለስ፣ እስራኤልም በምትኩ ፍልስጤማዊያን እስረኞችን ለመልቀቅ መታሰቡን ዘግበዋል።

እስራኤል በሃማስ በኩል ስለተሰጠው ምላሽ እስካሁን ምንም አይነት ሐሳብ ከመስጠት ብትቆጠብም፣ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የአሜሪካን ዕቅድ ስለመቀበላቸው ትናንት ለታጋች ቤተሰቦች ተናግረዋል።

በኢዮብ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review