ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረ አንድ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት የወረዳ ጽ/ቤት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

AMN – ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም

ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረ አንድ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የወረዳ ጽ/ቤት ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ከሰኔ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል መሸጋገሩ ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎ በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ በታገዱ ካርዶች የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ወረዳ 13 ጽ/ቤት የሆነ የነዋሪነት አገልግሎት ቡድን ኬዝ 2 የዲጂታል ምዝገባ ባለሙያ የነበረው አቶ ባጫ ኤጀታ ሃሰተኛ ሰነድ እያዘጋጀ መሆኑ ለክፍለከተማው የተቋሙ ጽ/ቤት በደረሰ ጥቆማ ባለሙያው በፀጥታ ሃይል ክትትል በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል።

በተደረገው ብርበራ ከተጠርጣሪው ጋር ህገወጥ ማነዋል መታወቂያ ብዛት 22 ፣ አንድ ያላገባ ማንዋል ካርድ፣ አንድ ማህተም እንዲሁም ከ100 በላይ የተለያዩ ሰዎች ፎቶግራፍ በኤግዝቢትነት ተይዞ በፖሊስ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review