ህብረተሰቡ በበዓል ወቅት ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል

You are currently viewing ህብረተሰቡ በበዓል ወቅት ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል

ህብረተሰቡ በበዓል ወቅት ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል

AMN – ሚያዝያ 9/2017

ህብረተሰቡ መጪውን የትንሳኤ በዓል ሲያከብር ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አስተዳደር፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፤ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲና ፣ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በመግለጫው እንዳሉት፥ ከተማ አስተዳደሩ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ህዝቡን የሚያረካና ከተማዋን የሚመጥኑ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ነው።

መጪው የፋሲካ በዓል ከአደጋ ነጻ በሆነ መልኩ እንዲከበር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።
በበዓላት ወቅት በቂ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲኖርና ሁሉም ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በተገቢው መንገድ እንዲሰጡ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተሰርተናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ በበኩላቸው፤ ህብረተሰቡ በዓሉን በሚያከብርበት ወቅት ድንገተኛ የእሳት አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ተቋሙ በበዓላት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችንና ለአደጋ አጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review