ህዝበ ሙስሊሙ የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ሲያከበረ ሀይማኖታዊ ስርዓቱ በሚያዘዉ መሰረት በመረዳዳትና በመተሳሰብ ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጎዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ መልእክት አስተላለፉ፡፡
ምክር ቤቱ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች አንኳን ለ1446ኛዉ አመተ ሂጅራ የአረፋ በዓል አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ፕሬዚዳንቱ፣ ነብዩ መሀመድ ባስተማሩት መሰረት የአረፋን ፆም በመፆም ከፈጣሪ ራህመትን መለመን ይገባል በማለት መልዕክት ማስተላለፋቸውም ተመላከቷል፡፡
በሀጅ ስነ ስርዓት ላይ መቆም ያልቻለ ምዕምን ይህንን መተግበር ይገባዋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በዓሉ በእለተ ጁመአ (አርብ) የሚዉል በመሆኑ ቀኑን ይበልጥ ልዩ ያደረገዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮችና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደረ ጋር በመተባበር፣ በዓሉ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል ብለዋል፡፡
በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመረዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅ እና ያለንን በማካፈል ከህዝበ ሙስሊሙ የሚጠበቅ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
በሩዝሊን መሀመድ