AMN – መጋቢት 8/2017 ዓ.ም
በጂቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ፣ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰኢድ ኖህ ሀሰን ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ህገ-ወጥ ስደት መቀነስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ኤምባሲው ከጅቡቲ ጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እና በህገ-ወጥ የደላሎች ሰንሰለት ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ሚኒስትሩ፣ ከኤምባሲው ጋር በቅርበት በመስራት አስፈላጊውን የህግ ከለላ በሚደረግበት ሁኔታ ላይም መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።