AMN – ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ህገ ወጥ ግብይቶችን፣ አዋኪ ድርጊቶችን እና ለመማር ማስተማር ሂደቱ እንቅፋት የሆኑ ወንጀሎችን በትኩረት በመቆጣጠር በከተማዋ አስተማማኝ ሠላም ማረጋገጥ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ከተገልጋዮች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የቢሮው ም/ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንደተናገሩት፣ በከተማዋ ህገ ወጥ ግብይቶችን ፣አዋኪ ድርጊቶችን እና ለመማር ማስተማር ሂደቱ እንቅፋት የሆኑ ወንጀሎችን በትኩረት በመቆጣጠር አስተማማኝ ሠላም ማረጋገጥ ተችሏል።
በሌላ በኩል በሩብ ዓመቱ በትራንስፖርት ዘርፉ ይታዩ የነበሩ ችግሮችንና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የሆኑ የተለያዩ ቅሬታዎችን ከህብረተሠቡ ጋር በመነጋገር መፍታት መቻሉንም ተናግረዋል።
በዓለሙ ኢላላ