“የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው” በሚል መሪ ሀሳብ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አካላት የመዲናዋን የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱም በቁርጠኛ አቋምና ውሳኔ የራስን አቅም እና ፀጋዎችን በመጠቀም፣ በከተማዋ ፈርጀ ብዙ የሆኑ የልማት ስራዎች መሠራታቸውንና ለአገልግሎት መብቃታቸውን በተጨባጭ ማየታቸውን ገልጸዋል፡፡
ለሀገርና ለትውልድ ሁለተናዊ እና ዘለቄታዊ እድገት የሚበጁ አስደማሚ ታሪካዊ ስራዎች መተግበር መቻሉን ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡
የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የተሠሩ የልማት ስራዎችን በማስተዋወቅ ፣የተዛቡ አመለካከቶችን በመመከት እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ሚናው የላቀ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል፡፡
በከተማዋ የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ በርካታና የተለያዩ የህዝብ መዝናኛ አገልግሎቶች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ተርሚናሎች፣ፖርኮች ፣ፕላዛዎች፣ የተለያዩ የንግድ ዘርፎችን ያቀፉ ማዕከላት ፣ታሪካዊ ቅርሶች እና አደባባዮች፣ የመኪና፣የእግረኛ እና የሳይክል መተላለፊያ መንገዶች ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እና ሠዉ ተኮር ፕሮጀክቶች ከተጎበኙ ልማቶች መካከል ናቸው።