ለመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 8ሺህ ኪሎ የሚመዝን የቴምር ድጋፍ ተደረገ

You are currently viewing ለመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 8ሺህ ኪሎ የሚመዝን የቴምር ድጋፍ ተደረገ

AMN – መጋቢት 13/2017

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመጎብኘት የ8ሺህ ኪሎ ቴምር ድጋፍ አድርጓል።

ቋሚ ኮሚቴውና ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የድጋፍና ክትትል ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መሆኑን የገለጸ ሲሆን እየሠራ ያለው ስራም የመንግስትን ሸክም ያቀለለና የሚመሰገን ተግባር መሆኑን አስታዉቋል፡፡

መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ስራውን በ40 ሰዎች በመጀመር በአሁኑ ሰዓት ከ8500 በላይ ሰዎችን በአዲስ አበባ እና በክልል ቅርንጫፎች በመርዳት ላይ የሚገኝ ሲሆን 2 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ሆስፒታል እና የአረጋዊያን ማረፊያም እየገነባ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review