በአሜሪካ ሜሪላንድ አንዲት ሴት ለሶስተኛ ጊዜ የ50 ሺህ ዶላር የሎተሪ ሽልማት ማሸነፏ ተነግሯል።
ባለ እድሏ በአሁኑ ሰዓት አስደሳች የህይወት ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ ገልፃለች።
በኦዊንግ ሚልስ ነዋሪ የሆነችው ሴት፣ ተጨማሪ ስጦታ ያላቸውን ሎተሪዎች እንደምትገዛ እና የዕጣውን አወጣጥ በየምሽቱ በስልኳ እንደምትከታተል ለሎተሪ አስዳደር ባለስልጣናት ተናግራለች፡፡
ሴትየዋ በፈረንጆቹ መጋቢት 29 ቀን 2025 የገዛችው ሎተሪ ግን የ50 ሺህ ዶላር አሸናፊ እንዳደረጋት ገልፃለች፡፡
ሴትየዋ ባለዕድል ስትሆን ከፈረንጆቹ 2000ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ይህኛው ዕድል ግን ከበፊቶቹ ከፍ ያለ እንደሆነ አመላክታለች፡፡
በቀጣይም ሌላ ዕድል አሸናፊ ለመሆን መዘጋጀቷን የገለጸችው ሴት፣ አሁን ባሸነፈችው ሽልማት የተለያዩ ወጪዎቿን እንደምትሸፍንበት እና በተረፈው ደግሞ እራሷን እንደምታዝናናበት መግለጿን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡
በወርቅነህ አቢዮ