ለቤት ውስጥ መገልገያነት ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ እቃዎች በልብ በሽታ ምክንያት ለሚከሰት ሞት መንስዔ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥናት አመላከተ

You are currently viewing ለቤት ውስጥ መገልገያነት ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ እቃዎች በልብ በሽታ ምክንያት ለሚከሰት ሞት መንስዔ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥናት አመላከተ
  • Post category:ጤና

AMN-ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም

ማክሰኞ የወጣ አንድ አዲስ ጥናት ፤ በውኃ ፕላስቲኮች፣ በምግብ ማሸጊያዎች፣ እና የተለያዩ ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ፕላስቲኮች በዓለም ዙሪያ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ የልብ ህመም ሞት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ አመላክቷል።

ኢ-ባዮሜዲስን በተባለው መጽሔት ላይ የወጣው ይህ ጥናት እንዳመላከተው፤ በ2018 በልብ ህመም ከሞቱ ሰዎች መካከል 368 ሺ 764 ወይም 13 በመቶ ለሚሆኑት ህልፈት ኬሚካሎች አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ደግሞ ከ55 እስከ 64 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ 10 በመቶ የሚሆኑት የዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎች ናቸው።

75 በመቶ የሚሆነው ሞት ደግሞ እስያ፣ መካከለኛው ምሥራቅ እና ፓስፊክን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች የተከሰተ ነው።

የጥናቱ መሪ እና የኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት ሣራ ሃይማን ፤ ፍታሌት የተሰኘው እና ፕላስቲኮች እንዲሳሳቡ የሚያደርገው ኬሚካል በሰው ልጅ ላይ ከፍተኛ አደጋ እንደሚያስከትል የሚያሳዩ በርካታ ማስረጃዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

ኬሚካሉ ለደም መፍሰስ፣ ለወንዶች መሃንነት፣ ለካንሰር፣ ከልክ በላይ ውፍረት እና ለከፍተኛ የደም ግፊት እንደሚያጋልጥ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡

በየካቲት ወር የወጣ ሌላ ጥናት ጥቃቅን ማይክሮፕላስቲኮች ወደ ሰው አንጎል ውስጥ በመግባት ደም ማነስ ሊያስከትሉ እንደሚችል መጠቆሙ ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል እንዳለው ከሆነ የተበከለ አየር ወይም ከፕላስቲክ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ምግቦች መመገብ ፍታሌት ለተሰኘው ኬሚካል ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

ተጋላጭነትን ለመከለካልም በተቻለ መጠን ፕላስቲኮችን ማስወገድ እና የታሸጉ ምግቦችን መቀነስ አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

በተጨማሪም የፕላስቲክ መገልገያዎችን በማይክሮዌቭ ውስጥ አለማስቀመጥ እና ምግብን በብርጭቆ፣ በብረታ ብረት፣ በሴራሚክ ወይም በእንጨት መያዣዎች ውስጥ ማስቀመጥም እንደመፍትሄ መቀመጡን ዩ ፒ አይ አስነብቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review