ለኅብረ ብሔራዊ ሀገሩ ቀናዒ የሆነ፣ ልማትን ዕውን ለማድረግ የወሰነ ትውልድ፣ ሰላሙንም በአስተማማኝነት ያፀናል – ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀ ስላሴ

AMN ኅዳር -29/2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀ ስላሴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ለኅብረ ብሔራዊ ሀገሩ ቀናዒ የሆነ፣ ልማትን ዕውን ለማድረግ የወሰነ ትውልድ፣ ሰላሙንም በአስተማማኝነት ያፀናል ሲሉ ገለጹ።

ፕሬዚደንቱ ለ19ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ ሲሉም የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

እኛ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ነጻነታችን የሚጋፋ ማንኛውንም የውጭ ኃይል በጋራ በማንበርከክ አንድነታቸን ጠብቀን ኖረናል ብለዋል።

ለኅብረ ብሔራዊ ሀገሩ ቀናዒ የሆነ፣ ልማትን ዕውን ለማድረግ የወሰነ ትውልድ፣ ሰላሙንም በአስተማማኝነት ያፀናል ሲሉም አክለዋል።

ካለመግባባት የምናተርፈው፣ ከልማት የምናጣው፣ ከሰላም የምናጎድለው እንደሌለ ከእኛ የተሻለ የተገነዘበ ሊኖር አይችልም ብለዋል።

ስለሆነም፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በዕኩልነትና በፍትህ መሠረቶች ላይ ይበልጥ በማፅናት ጠንካራ፣ የበለፀገች፣ የታፈረችና የተከበረች ኢትዮጵያን እንገንባ ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review