ለአዲስ አበባ ከተማ ልማት የከተማዋ ሕዝብ ያደረገው ትብብር ነዋሪው ለልማት ቅድሚያ የሚሰጥ ለመሆኑ ማሳያ ነው- የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት

You are currently viewing ለአዲስ አበባ ከተማ ልማት የከተማዋ ሕዝብ ያደረገው ትብብር ነዋሪው ለልማት ቅድሚያ የሚሰጥ ለመሆኑ ማሳያ ነው- የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት

AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም

ለአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ስኬት የከተማዋ ሕዝብ ያደረገው ትብብር ነዋሪው ለልማት ቅድሚያ የሚሰጥ ለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ስኬት የከተማዋ ሕዝብ ያደረገው ትብብር ነዋሪው ለልማት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ገልጸዋል፡፡

የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራው በውጤት ደረጃ ውሎ አድሮ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የኢኮኖሚ እና የኑሮ ሁኔታ በአጠቃላይ የሀገር ገጽታ የሚቀይር መሆኑንም ሚስትሯ ገልፀዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ተሞክሮ በመነሳት በመላው ኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች በተለይም የክልል ከተሞች የኢትየጵያን ትልቅነት የሚመጥን የከተማ ልማት መስራት እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራዎች በክልላቸው የአሶሳን ከተማ ጨምሮ በዞን እና በወረዳ ከተሞች የአዲስ አበባን የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነ የገለጹት ደግሞ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊን ሀሰን ናቸው፡፡

በመልሶ ማልማት ስራዎች የአካባቢን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የውስጥ አቅምን ተጠቅሞ መስራት እንደሚቻል ያሳየ የልማት ስራ ነው ብለዋል የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት፡፡

ጉብኝቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክት የማጠናቀቅ ባህል በክልሎች ለማስፋፋት የሚረዳ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

በሰው ተኮር የልማት ስራዎች ላይ ብልጽግና ባለፉት 6 አመታት የሰራቸው ልማቶች ከሀገር ውስጥ አልፎ ለሌሎች ሀገራትም ጭምር ፓርቲው ሰው ተኮር መሆኑን ማሳያ ነውም ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ለክልሎች ጉልበት የሚሰጥ እና ተሞክሮ የሚሆን እንደሆነም ጎብኝተናል ብለዋል የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review